@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
"ወልዲያ ያለው መከራ ከመነገር በላይ ነው በወልድያ የሚኖር አንድ ሰው አግኝተህ ከረሃብ በሕይወት እንዴት ተረፍክ፤ምን እየበላህስ እስከዚህ ደረስክ? ካልከው "አባቴ አባ ኤርምያስ እርሱ ተርቦ እያበላኝ፣እርሱ ተጠምቶ እያጠጣኝ " ይልኻል።
Tweet media one
Tweet media two
16
201
718

Replies

@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
የወልዲያ ሰው የዘመኑን ጴጥሮስ አግኝቷል።ይገርምኻል አባታችን በየባንክ ቤቱ የሚገኙ ጀነኔተሮችን ሰብስበው ወደ ወፍጮ ቤት በማስወሰድ፤ለክፉ ቀን ብለው ገንዘብ በቤታቸው ያስቀመጡ ባለሃብቶችን
1
3
29
@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
"እኔ እከፍላለሁ፣እኔ ባልኖር ቤተክርስቲያን ትከፍላችሗለች አይኔ እያየ ልጆቼ በርሃብ አይሙቱብኝ "እያሉ በተማጽኖ እየተበደሩ እህል ገዝተው እራሳቸው ብጹዕነታቸው ወፍጮ ቤት ቆመው እያስፈጩ እየመገቡ ነው።
1
2
33
@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
አቅም ኖሮት ሊያስፈጭ የሚመጣ ካለ እዛው ቆመው አንድ አንድ ኪሎ እያስቀነሱ በየቤቱ መንቀሳቀስ ለማይችሉ አረጋውያን ያደርሳሉ። ችግሩ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ጸሎተ ምሕላ እራሳቸው በዕንባ ሆነው እያደረሱ ነው።
1
2
28
@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
በአካባቢው ያሉ የሽብርተኛው ሕወሓት መሪዎችን ያሉበት ካንብም ሆነ ሌላ ቦታ በመሄድ ፊት ለፊት በመጋፈጥ "ልጆቼን አትንኩ ህዝቤን አታስጨንቁ እግዚአብሔር ይፈርዳል" እያሉ የህዝቡን መከራ እያቀለሉ ነው።
1
3
30
@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
ይገርምሃል ስለ አቡነ ጴጥሮስ እየሰማሁ ያደኩትን ታሪክ በገሀድ ተገልጦ በእርሳቸው ላይ አየሁት። ሞት አይፈሩም(ስለክርስቶስ የሞተ እንዴት ሞትን ይፈራል)። በከተማው ባሉ አቢያተ ክርስቲያናት ይዘዋወራሉ ያስተምራሉ።
1
4
33
@MuleFeTg
Mule FeTg (ኃይለ ሥላሴ)
3 years
እርግጠኛ ሆኜ የምንግርህ አቡነ ኤርምያስ ባይኖሩ ኖሮ የወልዲያ ህዝብ ይህንን የመከራ ዘመን ለመግፋት ይከብደው ነበር። "ለወዳጆችህ እንዲህ በልልኝ አቡነ ጴጥሮስን ማየት ከፈለጋችሁ ወልዳያ አለላችሁ በልልኝ " FB ሰፈር
0
5
45
@MeheretA1
ምሕረት🙏🏾 💚💛❤️
3 years
@MuleFeTg 🙏🏾
0
0
1
@maddy_asmare
Maddy Asmare
3 years
@MuleFeTg 🙏🙏🙏
0
0
1
@AsebeTeferi777
ጽnaት
3 years
@MuleFeTg ፈጣሪ ሆይ በቃ በለን። የወገን ሰቆቃ ያማል። #NoMore
0
0
4
@melesse_solomon
Melesse Solomon
3 years
@MuleFeTg በመከራህ ውስጥ ያልተለየህን ሰው ሁሌ አስብ! የቀራንዮ ጉዙ ስንቱን ይገልጣል መሰላችሁ!
0
0
3
@AbiA16072878
AxumAxum
3 years
Tweet media one
1
0
0
@Leah_ORG
Leah🔮
3 years
@MuleFeTg 🥺❤️
0
0
0
@proudlyEthio21
Ashu ወልደአብ 💚💛❤️
3 years
@MuleFeTg የሀይማኖት አባትነት በተግባር 🙏🙏❤❤
0
0
2
@KassegnS
Kassegn sirmollo
3 years
@MuleFeTg @melat_alebachew Ethiopia will win, this humbleness, this pride, this humanity we are out to show the world. We Ethiopians unite the world will not stop us. We must be stand tall. This picture mademy day, thank you
0
0
1
@ErkuHana
zagoche M
3 years
@MuleFeTg ብፁዕ አባታችን ቡራኪያችው ይድረስን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃቸው አሜን
0
0
1
@Knty2002
Tigist Solomon Abebe ኂሩተገብርኤል
3 years
@MuleFeTg እንደዚህ አይነቶቹን አባቶች ያብዛልን
0
0
1
@AhelamMuhamed
seada hassen
3 years
@MuleFeTg Allah yitebeklne wegenochachenen
0
0
0
@AW10574854
ፊታውራሪ
7 months
@MuleFeTg ወንድሜ የምትላቸውን ሁሉ አድርገዋል እሱን የካደ ሰው የለም። እስከመጨረሻው የሚፀና ግን የድል አክሊል ይቀዳጃል ይላል መፅሐፉ። አሁን አንተ አቡነ ኤልያስ ከሰው አራጅ ወታደር ጋር ተቀምጠው ያንን መናገራቸውን ትክክል ነው የምትለው?
0
0
0
@kidistZewdu22
kidistMesfin
7 months
@MuleFeTg Promoter!!!
0
0
0